About

We Are Non Profit Organization

ቤተ አማሀራ ወሎ አለማቀፍ መሀበር እንዲቋቋም ያስገደደን አንዱ ምክንያት በክልሉ ያለው ነዋሪም ሆነ ከሌላ ቦታ በማንነቱ ተፈናቅሎ የመጣው ህዝባችን ደርሶበት ያለውን ችግር ፣ሶቆቋ እና መከራ የሚጋራው መንግስትም ሆነ አካል ባለ መኖሩ ነው። ለውጡ በወገናችን ላይ ለውጥ ሆነበት ለባሰ እንግልት ፣ሞትና መፈናቃል ዳርጎታል። ከተለያየ አካባቢ በማንነቱ ሳቢያ ተገድሎ ፣ህይወቱ ተርፎ ወደ ክልላችን የገባው ወገናችንን መታደግ በአግባቡ ሳንችል ፥ በትግራይ ክልላዊ መንግስት እና በኢትዮጵያ መንግስት በተነሳው ጦርነት ሳዕቢያ ክልላችን ወደ 40 እና 50 አመት ወደኋላ እንዲመለስ ከማድረጉ ባሻገር በክልላችን የነበሩ ብዙ ተቋሞች ፣ትምህርትቤቶች ፣አብይተ ክርስቲያን ሳይቀር እንዲወድሙ ፣እንዲሁም ህዝባችን በራሱ ክልል ውስጥ ስደተኛ ቤት አልባ ፣ንብረት አልባ ሆኖ እንዲበታተንና በየመጠለያው ካፕ እንዲቀመጥ አድርጎታል
ይሄ ከንብረቱ ፣ከእርሻው ተፈናቅሎ ተበታትኖ ያለው ወገናችን በታላቅ ችግር ላይ ፣ረሀብ ላይ መሆኑን በማየት ለወገን ደራሹ ወገን ብቻ ነው በማለት ይሄን ወገናችንን አቅማችን በሚችለው ሁሉ ለመታደግ መሀበሩን መስርተን በመንቀሳቀስ ላይ እንገኛለን ። ወገናችን እጅግ መጠነ ሰፊ ድጋፍ እርዳታ ያሻል ፥ ብዙዎች ከሚሉት በላይ ወገናችን ታላቅ አደጋ እና ጉዳትም ላይ ይገኛል ። በመጠለያ ያለው ወገናችን በቀን አንድ ጊዜ እንኳን ለመመገብ ቅንጦት ሆኖበታል። እኛም እለት ከለት የበኩላችንን ለማዳረግ ደከመን ሰለቸን ሳንል እየጣርን እንገኛለን ። በዝህ አጋጣሚ ያለውን የሰጠ ንፉግ አይባልም እና ቤተ አማራ አለማቀፍ ድርጅት የምትችሉትን እርዳት ለወገናችሁ ትዘረጉ ዘንድ ይማጸናችኋል ፥ ድርጅቱንም በማገዝ አብሮ ለመሰራት የምትፈሉጉም ግለሰቦች ፣ድርጅቶችም ካላችሁ በራችን ክፍት ነው።

We Are A Strong Team

አማራነት ወንጀል በሆነበት ዘመን እኛው ለኛው ካልተሳሰብን ካልተረዳዳን አንተ ትብስ አንቺ ትብስ ካልተባባል ማንም የውጭ ሰው እናንተ ትብሱ ሊለን አይችልም ።እኛ ችግራችንን ለአለም ካላሳወቅን ፥ የወገናችንን እንባ ጠባቂ ካልሆን ፣ አቅማችን የፈቀደውን ያህል እጃችንን ካልዘረጋንለት  ሌላው ከኛ ውጭ የሆነ ሊረዳንም ሊረዳንም ፈጽሞ አይችልም ።እኛው የወገኖቻችንን ረሀብ ፣ስደት ፣መፈናቀል በችልተኝነት እጅ አጣምረን ካየን ፥እንዴት አለም ችግራችንን ሊያውቅልን ሊረዳን እና እርዳታ ሊለግሰን ይችላል?
አዎ . .በዚህ ዘመን አንድ ከመሆን፣ ለእርስበርሳችን ደራሽ ከመሆን ባሻገር ሌላ መፍትሄ የለንም ። አንድነተ ጥንካሬ ነው! ። እኛ አንድ ስንሆን ፣በጋራ ድምጻችንን ስናሰማ  የወገኖቻችንን እንባ ልናብስ ስንነሳ  በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የችግሩ መንስዔ የሆነ አካል እና አካሎች ትኩረት ሳይወዱ በግድ ሊሰጡን ይገደዳሉ ። አማራነት ወንጀል ሊሆን የቻለው እራሳችን የወገኖቻችንን እልቂት ፣ስደት ፣ሞትና እርዛት በቸልተኝነት በመመልከታችን ጭምርም ነው። ለህዝባችን መገፋት ፣መፈናቀል ፣ሞት ጭምር የኛ ዝምታ ትልቅ አበርክቶ አለውና ።

Become a volunteer

Join us for a better life and beautiful future

ለወገን ደራሽ ወገን ነው። እኛ አለንልህ ያላልነው ወገን ሌላው ሊለው አይችልም።እኛ ለወገናችን ድምጽ ካልሆንን ፣ለወገናችን እጅ ካልዘረጋን ፥ እራሳችንን ለመርዳት ካልተነሳሳን ሌላው ሊረዳን አይችልምና  ኑ በጋራ እንሰብሰብ ፥አለሁልሽ /አለሁልህ ወገኔ እንበለው !