Featured Causes
ልጆች ልጆች የዛሬ አበባዎች የነገ ፍሬዎች
ከምንም በላይ የልጆች መጎሳቆል ፣መሰደድ ፣መፈናቀል ፣አውላላ
ሜዳ ላይ ከመጣል የሚያክል ህመም የለም ። የአማራ ህጻናቶች
በማንነታችው ሳቢያ ለሞት ፣ልስደት ፣ለወላጅ አልባነት ተዳርገዋል
።በቅርብ በትግራይ እና በመንግስት መካከል በተደረገው
ጦርነት ሳቢያ ደሞ በክልል ውስጥ የሚኖሩትም ህጻናት
ከክልል ውጭ ከመጡ ህጻናት እኩል ቤት አልባ ፣ወላጅ
አልባ ሆነው በየ መጠለያው ተጥለው ፣ተፈናቅለው ይገኛሉ
።የነገ ፍሬዎቻችንን ለማዳን የእርሶ አስተዋጽዕ እጅግ ስለሚያስፈልግን በሚችሉት አቅም ልጆቻችን እንታደግ በማለት አለማቀፍ ቤተ አማራ ወሎ ጥሪዉን አቅርቦሎታል ።
ልጅ ያላባት ማሳደግ ከባድ ነው በተለይ ተፈናቅሎ ቤት አልባ ሆኖ
አማራዊ እህቶቻችን በተለያየ መልኩ ለዚህ አይነቱ ችግር በከፍተኛ ቁጥር ተጋልጠዋል ።በማንነት ከመገደል እስከ ጦርነት ሰለባ የመሆንና ልጆችን የብቸኛ ሀላፊዎች ብቸኛ ወላጅ እንዲሆኑ ተፈጥሮም ሰው ሰራሽ ችግርም አስገድዷችዋል።
ብዙዎቻችን አባት ፣እናት ተክዘው ተስፋ ቆርጠው ስናይ ልባችን ይሰበራ
ፎቶ ሺ ቃላት ይናገራል ይባላል። ብዙ
አማራ አባወራዎች በመጦሪያችው ዘመን
ንብረታችው ወድሞ ልጆቻችው ለአንድም
ለሌላ ሰለባ ሆነውባችው ጧሪ አልባ ወገን አልባ
ሆነው ተክዘው ተቆራምተው ከማየትበላይ
የሚያም ነገር የለም ። ላለፊት 35 አመታት
በአማራ ህዝብ ላይ ያነጣጠረው ችግር ፣መጎሳቆል
፣መፈናቀል ዛሬም ላይ ጦርነቱ ተደምሮበት
ከፍተኛ ቁጥር ያላችው አማራ አዛዋንቶች በየመጠለያ
ቦታ ተጥለው ይገኛሉ ።መቼም ከወላጅ ያልተፈጠረ የለም ።
አመት ባዕል ሲደርስ ከወላጅ ጋር ማሳለፍ ወላጅ ደስ እንዲለው ማድረግ መመኘት የሁላችንም ፍላጎት ነው። እስቲ የምንችለውን አድርገን ቢያንስ በቀን አንድ ጊዜ እንዲመገቡ እንርዳችው !
How you’re changing children’s lives
Health
እርሶ የሚሰጡት ምንም አይነት ስጦታ አይናቅም።ምንም እንኳን ለተሰደዱ ፣ለተፈናቀሉ ቤተሰቦች የመልሶ ማቋቋም ቤት መስራት ባንችልም ፣ነገር ግን እርሶ በሚሰጡን ምንም አይነት ድጋፍ ፥ ልጅቾ በቀን አንድ ጊዜ እንዲመገቡ ለማድረግ ያስችለናል። ከተፈጥሮ እና ከጦርነቱ ያመጣብን ችግር በላይ አያሌ ብዙ ህጻናቶች ለማለኔሪሽመት አደጋ ተጋልጠዋል ።
Education
Bete Amhara Wollo Books for Education
አለማቀፍ ቤተ አማሀራ ድርጅት ፣ለምግብ እርዳታ ከማሰባሰብ ባሻገር ፣
ለልጆች መማሪያ የሚሆን መጸሀፍቶችንም አበርክቷል ።ከናንተ ከደጋፊዎቻችን ጋር በመተባበር ፥ለልጆች የሚጠቅም የመማሪያ ቁሳቁሶችን ፣ደብተሮችን ለማቅረብ ከፍተኛ ስራ እየሰራ ይገኛል ።ምንም እንኳን ልጆቻችን ተሰደው ፣ቤት አልባ ሆነው በመጠላይ ቢገኙም ፣ የትምህርት ብቃተ ህሊናችው እንዲጎለበት ለማድረግ የበኩላችንን ለማድረግ ግድ ይለናል ።
Our Volunteers
Teferi Abegaz
Chairman
Seada Ali
Public affairs
Mohammed Ali
Vice Chairman
Kalkidan
Secretory